User:Shambel t./sandbox

From Wikipedia, the free encyclopedia

<<ታላቁ ደብር ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም>> (ክፍል 7) ¤4ኛ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር የተቆቁአመበት ታሪካዊ ቦታ ነው።ከዚህ ሌላ በዲማ የአብነት ትምህርት ቤት ውስጥ 6 የትምህርት ክፍሎች የሚገኙ ሲሆን እነርሱም የንባብ ቤት፣የዜማ ቤት፣የቅኔ ቤት፣የቅዳሴ ቤት፣ያቆቁአም ቤትና የትርጉአሜ ቤት ናቸው።ገዳሙ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ተምሮ የወጣ በርካታ ሊቃውንትን አፍርቷል።በየትምህርት ክፍሎቹ ተማሪዎችን የሚያስተምሩ ሊቃውንት አንድ ሴት መምህርጨምሮ በገዳሙ ይገኛሉ።ሆኖም ይህ አንድ የአገራችን ቅርስ የሆነ ታሪካዊ ቦታ ቀስ በቀስ እየተዳከመ በመሄዱ የአብነት ተማሪዎቹም በተለያየ ምክንያት እየቀነሰ የሄደበት ሁኔታ ተፈጥሮአል። @የገዳሙ ውጫዊ ገፅታ፦ የቆዩትን መንደሮች አቀማመጥና የቤቶች አሰራር ሲመለከቱ ድንገት የፍቅር እስከመቃብር ገፀ ባህሪዎች የበዛብህና ሰብለ ወንጌል ታሪክ ድቅን ይልብዎታል።በደራሲ ሀዲስ አለማየሁ በፍቅር እስከ መቃብር ውስጥ የተጠቀሱትን እልፍኝ እስከ አዳራሽ ስፋት ያላቸውን ትላልቅ የሳር ቤቶች ዛሬ ፈልጎ ማግኜት ይቸግራል በአሁን ሰአት የቆርቆሮ ቤቶች በዝተዋል አንድ የአንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት መንደሩ ውስጥ ይገኛል።.............እቀጥላለሁ

<<ታላቁ ደብር ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም>> ክፍል 6 ዲማ ለመንፈሳ ዊትምህርት ሀይማኖትንና ህግን፣መንፈሳዊ ስርአቶችን በስጋዊ በኩልም መልካም አስተዳደርን ሀገር ጥበቃ ስለ ሀገር የወገን ፍቅር ስለሀይማኖት ክብር መስዋእንነት እስከመክፈል የሚያበረክተውን እውቀት እና ትምህርት ለህዝብ ሲያስተምር የኖረ ሀገር ነው።በ5 አመት የጠላት ወረራ ዘመንም "ሀይንተ አበውኪ ተወልዶ ለኬ ደቂኤቅ"በአባቶች ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ የሚል ማሀተም አስቀርፆ የጀግኖች ማህበር አቆቁሞ አርበኞችን በተለያዬ መልኩ በመርዳት ከንጉሰ ነገስቱ ዘንድ ይመጡ የነበሩትን መልእክተኞች በመቀበልና ከሀገር ወደ ሀገር በማስተላለፍ ከፍ ያለ አስተዋፅኦ አበርክቷል።ጥላት ይሄን እንቅስቃሴ በማወቁ ዲማ የደረሰበት ስቃይ አሰቃቂ ነበር።ጥላት በቆየበት አመታት ሁሉ የከባድ መሳሪያዎች የተኩስ አላማ ከማድረግም በላይ በተለይም ለ45 ቀናት በየቀኑ 6እና7 አውሮፕላኖች እየተመላለሱ በቦንብ ደብድበውታል።ቤተክርስቲያኑን ከቦምብና ከመድፍ ውርጅብኝ ተርፎ ያርበኞች መጠጊያ ሆኖ በታምራት ሲድን አካባቢው በሰማይና በምድር በተደረገበት ወረራ ብዙ ህዝብ አልቁአል ቤቱተ ቃጥሏል፣ንብረት ተዘርፏል። ¤ዲማን ሊገልፅ የሚችሉ ነገሮችን ለመግለፅ ያህል፦

  • 1ኛ በአብነት ትምህርት አሰጣጡ ያኔ በዚያ ዘመን ትምህርት ባልተስፋፋበት ጊዜ እንደ አንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቁአም ከሀገራቱ ከጫፍ እስከ ጫፍ ለሚመጡ ተማሪዎች እውቀትን ሲያገበያይ የኖረ ገዳም ነው።
  • 2ኛ በአከናወናቸው ማህበራዊ ሚናዎቹ ገዳሙን ዝነኛ አድርጎታል።
  • 3ኛ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንደሚያውቀው አንጋፋው ደራሲ ዶክተር ሀዲስ አለማየሁ የቀድሞው ዲማና አካባቢውን ህያው በሆነ አቀራረቡ ያብነት ትምህርት ቤቱን አስደግፈው አስቀኝተውታል።
  • 4ኛ............... እቀጥላለሁ

<<ታላቁ ዲማ ደብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም>>


ክፍል 5 አስተዳደሩም ማህበረሰቡን በ4 መድበውታል። ይህም፦ ¤የሹም ሽርቤት ¤የቂኤስ ቤት ¤የመሪቤት ¤የጨዋ ቤት

  1. 1ኛ የሹም ሽር ቤት፦የሹም ሽር ቤት የሚባለው ለደብርነት ማእረግ በቅኔ ማህሌት እያገለገሉ ስለ ሀገር ጉዳይ ሲወጡ ሲወርዱ ቆይተው በውል ተመርጠው የተለያዩ ሹመት የተሰጣቸው ናቸው።ይህም የተሾሙትንና የተሻሩትን ያጠቃልላል።
  2. 2ኛ የቂኤስ ቤት፦የቂኤስ ቤት የሚባሉት ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ከቤተ መቅደሱ በድቁና፣የቅኔ ማህሌት፣ሳህታት እየቆሙ ከበሮ በመምታት መቁአሚያና ፅናፅል በማቀበል ሲያገለግሉ አድገው አካለ መጠን ሲደርሱ መንኩሰው ከቤተ መቅደስ በቅዳሴ የሚያገለግሉ ናቸው።
  3. 3ኛ የመሪ ቤት፦የመሪ ቤት የሚባሉት ከእዚህ በላይ በተመለከተው መሰረት አድገው ንጉስ ነን አንፈልግም ብለው ሚስት አግብተው ቤት ሰርተው በቅኔ መሀሌት እያገለገሉ ለአገር ጉዳይ ሲወጡ ሲወርዱ የሚመሩ መምህራን ናቸው።
  4. 4ኛ የጨዋ ቤት፦ዲማ ውስጥ የተወለደ ልጅ ሁሉ በ4 አመቱ እንደ ደንብ ሆኖ ከተማሪ ቤት ሳይገባ አይቀርም።የጨዋ ቤት የሚባለው በዚሁ መሰረተ ትምህርት ቤት ገብቶ ትምህርት እድሉ ሳይሆን ይቀርና ትምህርርቱን አቁአርጦ እርሻና በንግድ የሚተዳደረው ነው።ይህ ማህበረሰብ የጭዋ ልጅ ተብሎ እርስቱን ይዞ ቤተክርስቲያንን እየደገፈ ይኖራል።ስለዚህ የዲማ አስተዳደር ዲሞክራሲያዊ ቀመስ ነበር ማለት ይቻላል።ማናቸውምንም የአገር ጉዳይ እነዚህ የማህበረሰብ ክፍሎች መክረውበት የሚፈፀም እንጂ በተናጠል አይሰሩም።ህዝቡ የሚተዳደረው በመረጣቸው ልጆች ስለሆነ በየ3 አመቱ ምርጫ እያደረጉ በየደረጃው እየሻሩና እየሾሙ ይኖሩ ነበር።..............እቀጥላለ

<<ታላቁ ደብር ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም>> ክፍል 4 ¤በገዳሙ ዙሪያ አካባቢ የሚገኙ የተለያዩ አስደናቂ ስፍራዎችና ገፀ በረከቶች 1ኛ የጊወርጊስ ፈረስ ማሰሪያ፦ከዋሻው ትንሽ ዝቅ ብሎ ከእድሜ ብዛት የተነሳ በመድረቅ ለይ የሚገኝ ገመድ መሰል የሀበሻ ፅድ ይገኛል።ይህ ፅድ የጊወርጊስ ታቦት ዋሻው ከገባ ጀምሮ የጊወርጊስ ፈረስ ማሰሪያው ነው ተብሎ በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ ይታወቃል። 2ኛ የጊዮርጊስ የፈረስ ኮቴ፦ከዋሻው መግቢያ ትንሽ ከፍ ብለን አንድ የሆነ ክስተት የፈጠረው የሚመስል ጉድጉአድ አለ ስለዚህ ቦታ የሀይማኖት አባቶችን ጠይቀን የሚያስረዱት ነገር የጊወርጊስ ፈረስ ኮቴ ነው ይላሉ።ለዚህ የፈረስ ኮቴ መፈጠር ምክንያት ምን እንደሆነ የሀይማኖት አባቶች ሲያስረዱን በዚህ ታሪክ በተፈጠረበት ዘመን አካባቢ በጥቅጥቅ ደኖች የተሸፈነ ነበር።በገዳሙ ይኖሩ የነበሩ መነኮሳትን የሚያስቸግሩ ወንበዴዎች ይኖሩበት እንደነበረና ከዚያም በመነሳት እስከ አሁን ድረስ መነኩሴ አሩጥ በመባል የሚጠራ ቦታ በአካባቢው ይገኛል።በመሆኑም አንድ ቀን አንዲት ሴት መነኩሴ ብቻዋን በመንቀሳቀስ ላይ በነበረችበት ወቅት ወንበዴው ሲመጣ የጊወርጊስ ያለህ እያለች አዳኝ ስትማጠን በዚህ ቀዳዳ በኩል ጊዮርጊስ መጥቶ አድኗት በቀዳዳው በኩል እንደተመለሰ የሀይማኖት አባቶች በልበ ሙሉነት ይናገራሉ።..............እቀጥላለሁ

<ታላቁ ደብር ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ 3>> የዚያን ጊዜ የየአድባራቱ ቀሳውስት እና ሊቃውንት ታቦቱን ለማንሳት ተቀዳደሙ።ታቦቱ ግን እንደ ድንጋይ ሆኖ አልነሳም አለ።በዚያን ጊዜ የዲማ መስራች አባ ተከስተ ብርሀን ቀረብ ብለው ቢያነሱት እንደገለባ ሆነላቸው።ንጉሱም ይሄን ሲያዩ ተገርመውና ደስ ብሎአቸው ለእሳቸው የሚቀመጡበት በቅሎ፣የእራስ ቆብ፣ሰንተል፣ነጋሪት፣እራስ ማሰሪያ፣ከመንግስታቸው ሴሶ የገዳሙን መብት ደግሞ የአፄ ፍንታ(በገዳሙ ለይ የማይወስኑ አፄዎች አስደርገው ሰደዷቸው)ይባላል።ታቦቱም እንደመጣ ዋሻ የገባ መሆኑ ይነገራል።ይህም የሆነበት ምክንያት በወቅቱ አሁን ዲማ ያለበት ቦታ ይታወቅ ስላልነበረ በስአቱ የነበረውን ቤተ ክርስቲያን አሁን ባለበት ቦታ ከተሰራ በሁአላ ይህንን ታቦት ለመውሰድ የተሞከረ ቢሆንም ተመልሶ ወደ ዋሻ እንደሄደ እና አሁንም ድረስ በረድኤት ዝክሩ እለት ማለትም ሚያዝያ 23 ቀን ከባድ ንፋስ ይታያል።ይሄም ታቦቱ በእራሱ ሀይል ተመልሶ ወደ ዋሻው ቤተክርስቲያን ሲሄድ ነው ተብሎ ይታመናል።አቡነ ተከስተ ብርሀን መለኮሳትን አስከትለው ዲማ ገብተው ታቦተ ማርያምን ይዘው በአንዱ ዋሻ ውስጥ ተቀመጡ።እርሳቸው ከአለፉ በሁአላ አቡነ ቶማስ ተተኩ አቡነ ቶማስም በአፄ ይሳቅ ዘመነ መንግስት ታቦተ ጊወርጊስን ከዋሻው ወስደው ዲማ ተከሉ የተከሉትም በገዳም ስርአት ነበር።መነኮሳቱም በገዳም ስርአት እየተመሩ ህዝቡንም በአንዱ በኩል በአለማዊ ስርአት እየመሩ እስከ 7ኛው መምህር አቡነ ተክለ አልፋ ድረስ ቆይቷል።በዚህ ወቅት የግራኝ ወረራ ዘመን አልፈው ከስደት ሲመለሱ መለኮሳቱ በፍቃዳቸው ወደ ገዳምነት ወይም አንድነት ይቀየርልን ሲሉ ለመኗቸው።አቡነ ተክለ አልፋም የመለኮሳቱን ልመና ተቀብለው ለአስተዳደሩም ስርአተና ደንብ አወጡለት።.................. እቀጥላለሁ

<<ታላቁ ደብር ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም 2>> ይህ ታሪካዊ ገዳም በውስጡ ብዙ የተለያዩ በርካታ ቅርሶችን ይዟል። ጥቂቶቹም፦ ¤የአፄ ዮሀንስ አራተኛ ዘውድ፣ ¤የወርቅ መስቀል፣የአፄ ይሳቅ የወርቅ ጫማ፣ ¤የእባብ ቅርፅ ያለው የወርቅ ዘንግ፣ ¤በስእል የተንቆጠቆጡ አርባእቱ ወንጌል እና ገድለ ጊወርጊስ፣ ¤የንጉስ ተክለ ሀይማኖት ጦር፣ ¤የራስ መኮነን ካባና ሌሎች ምስጢራዊ ቅርሶች የሚገኙበት ጥንታዊ ገዳም። የዲማ የመጀመሪያ ታላቁአ ገዳም ማርያም ነበረች ይባላል።ከእዚህ በሁአላ በአፄ ዳዊት የክርስቶስን መስቀል ከግብፅ ሊያመጡ እንደሄዱ ታቦት ንዋሌ ስም ይዘው እንደመጡና ወደ ሀገራቸው ሳይመለሱ ከመንገድ እንደሞቱ ከአባቶች ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።ልጃቸው አፄ ይሳቅ ባሉበት ተፈልገው ከነገሱ በሁአላ የጊወርጊስን ታቦት ከመስቀሉ ጋር ወደ ሀገራቸው አስገቡ በመሆኑም ይህ ከመስቀሉ ጋር የመጣው ታቦት ወደ ሀገራቸው ከአስገቡት በሁአላ በጊዜው ወጅ ይባል ከነበረ በተለይ ከደረሰ በሁአላ የሚያንቀሳቅሰው ጠፋ።ንጉሱም በሁኔታው ተገርመው የፈቀደላቸው ይህንን ታቦት እንዲያነሱት በአዋጅ ያስነግራሉ።................. እቀጥላለሁ ‘’